በቅርቡ ወደተግባር ሊለወጡ እየተሰራባቸው የሚገኙ ሥራዎች
ውድ የቅዱስ ያሬድ ቤተሰቦች ሰላም ለእናንት ይሁን!
ኢትዮጵያ ያአሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት የቅዱስ ያሬድን አስተምህሮ የተግባራዊ ልምምዳችን አካል ለማድረግ ለሚያደርገው ጥርጊያውን የሚያቀኑ ሁለት ዐበይት የፕሮጅክት ሀሳቦችን መተግበር ይጀምራል።
ውድ የቅዱስ ያሬድ ቤተሰቦች ሰላም ለእናንት ይሁን!
ኢትዮጵያ ያአሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት የቅዱስ ያሬድን አስተምህሮ የተግባራዊ ልምምዳችን አካል ለማድረግ ለሚያደርገው ጥርጊያውን የሚያቀኑ ሁለት ዐበይት የፕሮጅክት ሀሳቦችን መተግበር ይጀምራል።
አምስቱ ጸዋትወ ዜማ በመባል የሚታወቁት የቅዱስ ያሬድ ስራዎች ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬና መዋስዕት ናቸው፡፡ እነዚህም በሰከንድ፣ በደቂቃ፣ በሰዓት፣ በቀን፣ በወራትና ዓመት ቀመር የግዜ ወሰን ተበጅቶላቸው ከዓመት ዓመት የሚደረሱ ጣዕመ ዜማዎችና ምንባባት ሲሆኑ ድርሰቶቹ ግጥማዊ ምት ያላቸው/Poetic፤ የትውን ጥበብ አላባውያን ጎልተው የሚስተዋልባቸው ክዋኔ ጥበባት ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ስነውበት እና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት
1. እንደ ሀሳብ
ኢትዮጵያ አጅግ በጣም ጥንታዊት፣ ትውፊታዊትና ባህላዊት አገር ነች፡፡ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤትና ቀደምት ምድር፡፡ ቀደምትና ጥንታዊ ስልጣኔ የናኘባት አገር ከሆነች ታዲያ እንደምን አሁን የዓለም ጭራ ሆነች የሚለው ጥያቄ እጅግ የሚያብከነክን ጥያቄ ነው፡፡ ሁሉም በተለያየ አጋጣሚ ጥያቄውን እያነሳ ዘመናት ተቆጠሩ፤ እኛም ዛሬ ይህንንው እንጠይቃለን፡፡
ይህ ቤተሰብ በኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት (Ethiopian St. Yared’s Philosophy, Wisdom, Aesthetics and Arts Enrichement Organization) ድርጅት ተመሥርቷል።
ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮጵያና ትውልድ የናኘው ትሩፋት በውል ታውቆ ኢትዮጵያ ቅዱስ ያሬድ በዘመኑ የናኛትን ወርቃማ ዘመን ማምጣትና በእሱ ፈለግ ኢትዮጵያን ሰው የሚኖርባት አገረ እግዚአብሔር ማድረግ ነው፡፡
ስለቅዱስ ያሬድ የሚያወሱ በርካታ መጻሕፍትና ጥናታዊ መጣጥፎች አሉ፡፡ በርካታዎቹ ከውልደት በአካለ ስጋ ተለየ እስከሚባልበት ግዜ ድረስ ያለውን ሂደት ስለቅዱሱ የሚያወሩትን ጥንታዊውን ድርሳን፣ ገድልና ስንክሳር መሠረት አድርገው ሲጽፉ ጥቂት ምንባባት ግን ውልደቱን በተመለከተ የተለየ ወቅት ሲጠቅሱ ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ ቅዱስ ያሬድ ነበረበት ከሚባለው ዘመን እና የነገስታት ታሪክ ጋር የተጠቀሱት ማህበራዊ እውነታዎች የማይጣጣሙና በእጅጉ የተፋለሱ ሆነው በመገኘታቸው የቅዱስ ያሬድን ድርሳን፣ ገድልና ስንክሳር መሠረት ማድረግ ግድ ይላል፡፡
ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያ በማናቸውም ምድራዊና ሰማያዊ እውቀትና ጥበብ ረሀብ ዐይኖቿ በቅልውጥ ሩቅ እንዳያንጋጥጡ የደለበ ትሩፋትና በረከት ሰጥቷታል፡፡ ጥበብ ምድራዊ ጥበብ ሰማያዊን ናኝቷታል፡፡ ይሁን እንጂ የምርጫ ጉዳይ ይሁን አለማወቅ ኢትዮጵያ ታች ወርዳ ከጨቅላ የአውሮፓና ምዕራባዊ አገራት የእውቀትና የትምህርት ፈሊጥ ማምጣቷ አልቀረም፡፡ ይህም ብቻ ሳይበቃ ደግሞ የራሷን እንደሌለ በመቁጠር ሊቃውንቶቿን የአውሮፓ እውቀት፣ ጥበብና ፍልስፍና ቅኝ ተገዢ የምታደርግበትን የትምሕርት ሥርዓት ተቀብላና ቀርጻ ራሷን አንቆ በመግደል የማጥፋት ያህል አበክራ የሰራች አገር ለመሆኗ ገሀድ ነው።