የቅዱስ ያሬድ ቤተሰብ ግብ እና ዓላማ

admin
Feb
27
2024
  1. ግብ

ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮጵያና ትውልድ የናኘው ትሩፋት በውል ታውቆ ኢትዮጵያ ቅዱስ ያሬድ በዘመኑ የናኛትን ወርቃማ ዘመን ማምጣትና በእሱ ፈለግ ኢትዮጵያን ሰው የሚኖርባት አገረ እግዚአብሔር ማድረግ ነው፡፡

  1. ዓላማ

በቅዱስ ያሬድ አስተምህሮና አገር በቀል እውቀት የራሷን እውነት የምትኖር ኢትዮጵያን መፍጠር ነው፡፡ በእውቀትና በጥበብ የተቃኘ ምክኛታዊ ትውልድ ተፈጥሮ ለማየት በጥናት፣ በምርምርና በእውቀት የታገዙ ምክረ ሀሳቦችን እያዘጋጀ የልጆቻችንን ኢትዮጵያ ለመስራት የሚደረጉ ጥረቶችን በመደገፍና በማስፋፋት  የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረግና አዎንታዊ ጫና መፍጠር ነው፡፡ ለዚህም የቅዱስ ያሬድን የልደት እና የእረፍት ቀን ምክንያት በማድረግ ሚያዝያ 5 እና ግንቦት 11 ቀን፤ የቅዱስ ያሬድ ጥበብና አስተምህሮ የሚናኝበት በዓመት ሁለት ግዜ ታላላቅ ማህበራዊ ፌስቲቫሎችን በማዘጋጀት የኝዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞችን እውን ያደርጋል።

ቤተሰብ ጠንካራ ማሕበራዊ ተቋም ሲሆን ምናልባትም አገር ለመለወጥ አዳዲስ አስተሳሰቦችን በማስረጽና ሰላማዊ፣ በእውቀትና በጥበብ በተቃኘ ሕብረት ማሕበራዊ ንቅናቄ መፍጠር የቤተሰቡ ዓላማ ነው፡፡

  1. ዝርዝር ዓላማ
  • ከቤተሰቡ በሚደረገው የምዝገባና ዓመታዊ መዋጮ ቤተሰቡ የቅዱስ ያሬድን ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ለማስፋፋት በድርጅቱ የታለሙ ተቋማትን ለመገንባት አስተዋጽዖ ያደርጋል።
  • የቅዱስ ያሬድን አስተምህሮ ተቋማዊ ለማድረግ በሀሳብ፣ በእውቀት፣ በጉልበትና በገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ጠንካራ ቤተሰብ እንዲኖር ማድረግ፡፡
  • የቅዱስ ያሬድን እውቀቶችና ፍልስፍናዎች ለማስተዋወቅና ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ በወርክሾፕ፣ በሴሚናር፣ ዐውደ ርዕይ በማዘጋጀትና የተለያዩ የፕሮጀክት ሀሳቦችን በማመንጨት አዋቂ ትውልድ እንዲፈጠር እና የቅዱስ ያሬድን የጥበብ ማዕከላት መገንባትና ማስፋፋት፤ በኃላፊነት ስሜት ዳር ማድረስ፡፡