የቤተሰቡ ተቋማዊ ቅርጽ

admin
Feb
27
2024

ይህ ቤተሰብ በኢትዮጵያ ያሬዳዊ ፍልስፍና፣ ጥበብ፣ ሥነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ማበልጸጊያ ድርጅት (Ethiopian St. Yared’s Philosophy, Wisdom, Aesthetics and Arts Enrichement Organization) ድርጅት ተመሥርቷል።

የቅዱስ ያሬድን ቤተሰብ የሚጠብቁ (Gardian of the family) አባወራ እና እማወራ ይሾማሉ፡፡ መሥራች አባላትን የያዘ የቤተሰብ ሸንጎ በ120 የጌታ ቤተሰቦች ምሳሌ በቁጥር 120 የቤተሰቡ የበኩር ልጆች የቤተሰብ ሸንጎ ይሆናሉ፡፡ ከውስጣቸው ሸንጎውን የሚመሩ ሊቀ መንበር፣ ጸፊና ሌሎች አስፈላጊ አባላትን መርጠው ይሾማሉ፡፡ የሁሉም የሥራ ዘመን ሦሥት ዓመት ሆኖ ሸንጎው በሦሥት ዓመቱ የሚያስተባብሩትን መሪዎች እየመረጠ ይሾማል፡፡